ሚያዝያ 2 /2015 (አንካራ)
በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሀመድ በቱርኪዬ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ አስር ባለሀብቶች ጋር በሀገራችን ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮች አስመልክቶ በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አካሄደዋል ።
በውይይቱም ከኤፕሪል 26-28 ቀን 2023 በአገራችን ስለሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ፣በሀገራችን ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ፣ መንግስት በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ለውጭ ኢንቨስተሮች እያደረገ ስላለው ማበረታቻዎች አስመልክቶ በፓወር ፖይንት በተደገፈ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።
ባለሀብቶቹም በበኩላቸው በቱርክ የተለያዩ ካምፓኒዎች እንዳሉዋቸው ፣ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እያደረጉ እንደሆነ በማንሳት በቀጣይም በአገራችን በሚዘጋጀው ፎረም ላይ ለመሳተፍ እና በአገራችንም ያሉት ኢንቨስትመንት አማራጮች ለማየት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል ፡፡