ግንቦት 22 /2015 (አንካራ)

በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሐመድ በቱኪዬ ኮኒያ በግብርና ዘርፍ ማሽኖች በማምረት የሚታወቀው ABOLLO ካምፓኒ CEO ከሆኑት Tevfik GUMUS እና ከሌሎች የድርጅቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም በአገራችን በግብርናው ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ስላለው ምቹ ሁኔታና መንግስት በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ የውጭ ኢንቨስተሮች እያደረገ ስላለው ማበረታቻዎች አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።

የኩባንያው ባለቤቶችም በበኩላቸው ኩባንያው ከ50ዓመታት በላይ የእርሻ መሳሪያዎችን የማምረት ልምድ እንዳለው፣ ምርቱን ለ 40 የተለያዩ አገራት እንደሚልክ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ 20 የሚደርሱ የአፍሪካ አገራት እንደሚልክ፣ በካዛኪስታን TEKYATAGANLİ በሚል ስያሜ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ እንዳላቸው ፣የአይሶ ሰርተፍኬት ተሸላሚ እንደሆነ፣ በቀጣይ እ.ኤ.አ. በ2024 በአገራችን ዘመናዊና ለአገራችን ተስማሚ የሆነ የእርሻ መሳሪያዎች እና ትራክተሮችን ለማምረት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ወር ለቅደመ ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ አገራችን መግባት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram