ታህሳስ 01 ቀን 2016 ዓ.ም (አንካራ)

በቱርኪዬ የሚገኘው የኢፌዲሪ ሚስዮን በቱርኪዬ የአምባሳደሮች ባለቤቶች አንድነት ማህበር (DMEDD) በአንካራ ሸራተን ሆቴል ባዘጋጀው የባህል ባዛር ላይ ከአገራችን የቡና አምራች እና ላኪ ከሆነዉ ሀንሰን ቡና ጋር በጋራ ተሳትፎ አድርጓል።

በባዛሩ ላይ ቡና የማቅመስና በሀንሰን በኩል የተለገሰ ለበጎአድራጎት አገልግሎት የሚውል የቡና ሽያጭ ተከናዉኗል። ከዚህ በተጨማሪ ባህላዊ የቡና አፈላል ስርዓት በማዘጋጀት ለተመልካቾች ማስተዋወቅ ተችሏል።

ሀንሰን ቡና በሀገራችን እሰፔሻሊቲ ቡና አምራች እና ላኪ ድርጅት ሲሆን ለወደፊቱ የሀገራችንን ቡና በቱርክዩ ገበያ ለማስተዋወቅ ከሚስዩኑ ጋር በትብብር እንደሚሰራ በተደረገዉ ዉይይት መግባባት ላይ ተደርሳል።

ይህ ባዛር በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ዋና አላማውም ለበጎ አድራጎት የሚውል ገንዘብ ማሰባሰብ ሲሆን፣ በዘንድሮው ባዛር ላይ ከ40 በላይ አገራት ተሳትፈዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram