የካቲት 29 /2015 (አንካራ)

በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሐመድ በቱርክ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር በሀገራችን ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮችን አስመልክቶ በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አካሂደዋል።በውይይቱም በሀገራችን ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ መንግስት በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ለውጭ ኢንቨስተሮች እያደረገ ስላለው ማበረታቻዎች አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።

ባለሀብቶቹም በበኩላቸው በቱርክ የተለያዩ ካምፓኒዎች እንዳሉዋቸው ፣ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እያደረጉ እንደሆነ በማንሳት፣ በቀጣይም በአገራችን በግብርናው፣ በኢነርጂ፣ በኮንስትራክሽን፣ በትራንስፖርትና በሆቴልና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ፣ በቀጣይ ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ሀገራችን ለመግባት ፍላጎት እንዳላቸው መረዳት ተችሏል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram