ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም (በአንካራ የኢፌዲሪ ሚስዮን)- በክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የልዑካን ቡድን አንካራ የሚገኘውን የኢፌዲሪ ኤምባሲን በመጎብኘት ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የልዑካን ቡድኑ አባላት በሚስዮኑ ቅጥር ግቢ ሲደርሱ የኤምባሲው ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በውይይቱ ወቅት በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ የዕንኳን ደህና ጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ አጠቃላይ የሚስዮኑን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ በበኩላቸው አገራችን እየተከተለች ያለችውን የውጭ ግንኙነት አካሄድ እና መ/ቤቱ እያካሄ ስላለው የማሻሻያ ስራዎች አስመልክቶ ማብራሪያ በመስጠት ዲፕሎማቱ መንቀሳቀስ ያለበት የአገራችንን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ መሆን እንዳለበት አጥንኦት በመስጠት የገለጹ ሲሆን ወደፊት በትኩረት ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ክብርት ያስሚን ወሃብረቢ በበኩላቸው ስለ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መ/ቤት ምንነት እና አሰራር ገለጻ በማድረግ በቱርኪዬ ያለውን የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት(FDI) እምቅ ኃይል ከመጠቀም አኳያ ከሚስዮኑ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram