ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም (አንካራ)
በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሐመድ በቱርኪዬ የአንካራ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ከሆኑት Mr. Gursel BARAN ጋር በፅ/ቤታቸዉ በመገኘት ውይይት አደረጉ።
በውይይቱም ክቡር አምባሳደር አደም በሀገራችን እና በቱርኪዬ መካከል ስላለው ግንኙነት፣ በአገራችን ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ለሀገራችን ምርቶች ገበያ ማፈላለግ በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ በማድረግ የቱርኪዬ ባለሀብቶች አገራችን ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት አስቻይ ሁኔታዎች እንዲያዩ፣ በሀገራችን በሚካሄዱ የንግድ ባዛሮች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉና በቀጣይ ምክር ቤቱ ከኤምባሲው ጋር በጋራ በመሆን የቢዝነስ ፎረም እንዲያዘጋጅ ጥያቄ አቅርበዋል።
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው በተደረገላቸዉ ገለፃ አመስግነዉ ቱርኪዬ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የአፍሪካ አመት ብሎ በመሰየም ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንና በቱርኪዬ (አንካራ) ያለውን የኢንቨስትመንት ፣ የንግድና ቱሪዝም አቅም አስመልክቶ ማብራሪያ በመስጠት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ሚዛኑን እንዲጠብቅ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል ፡፡
የአንካራ የንግድ ም/ቤት 1923 የተመሰረተና ትልቁ መንግስታዊ ያልሆነ ከቱርኪዬ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ተግባራትን የሚያከናዉን ተቋም ነዉ።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram