ህዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም (አንካራ)

በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሐመድ አንካራ ከተማ የሚገኘው MTA International Mining Incorporated Company (MTAIC) ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ Dr. Nail Yildirim እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎችን በፅ/ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋል።

በውይይቱም Dr. Nail MTAIC በማእድን ፍለጋ፣ ምርምርና ማምረት ዘርፍ የተሰማራ መንግስታዊ የሆነ ድርጅት መሆኑን በመግለፅ ቱርክዩ እና ሀገራችን በማዕድን ዘርፍ በጋራ ለመስራት በአደረጉት ስምምነት መሰረት በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ እና ሚስዩኑም ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

ክቡር አምባሳደር በበኩላቸዉ ቀደም ሲል በተፈረመዉ ስምምነት መሰረት ወደ ተግባር መግባት ጠቃሚ መሆኑን በማንሳት በዘርፉ በሀገራችን ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ አድርገዋል።

MTA International Mining Inc. በአንካራ የተቋቋመ በቱርኪዬ ሪፐብሊክ ኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር በመወከል የማዕድን ምርምር፣ ፍለጋ እና ሌሎች ተግባራትን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያከናዉን እኤአ በ2019 የተቋቋመ ድርጅት ነው።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram