ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም (አንካራ)

በቱርኪዬ የኢ,ፌ.ዲ.ሪ. ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ ታዋቂ ባለሃብት የሆኑት እና በኢስታንቡል ከተማ የኢ,ፌ.ዲ.ሪ. የክቡር ቆንስል ተደርገው አዲስ የተሾሙትን Inan Altinbas በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በማነጋገር የሹመት ደብዳቤያቸውን አስረክበዋል፡፡

የክብር ቆንስሉ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ እንዲሁም የአገራችንን ዜጎች መብት እና ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ሊሰሩ በሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በተጨማሪም የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ እንዲያጠናክሩ መመሪያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ የክብር ቆንስሉ በበኩላቸው የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram