ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም (አንካራ)

በቱርኪዬ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ በቱርኪዩ የሱዳን ሪፐብሊክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ከሆኑት ናዲር ዩሲፍ ኤልታይብ ጋር በአገራቱ ሁለትዮሽ ግንኙነት እና በወቅታዊ የሱዳን ጉዳይ ላይ ዉይይት አደረጉ።

ክቡር አምባሳደር አደም ለሱዳኑ አቻቸዉ በሱዳን በተፈጠረው ግጭት ማዘናቸዉን በመግለፅ፣ ኢትዮጵያ ግጭቱ በዉይይት እንዲፈታ የምትፈልግ መሆኗን እና አገራችን በቅርቡ ያደረገችውን ውጤታማ የግጭት አፈታት ስርዓት እንደ ተሞክሮ አቅርበዋል።

የሱዳኑ አምባሳደር በበኩላቸዉ ወቅታዊ የሱዳንን ሁኔታ በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግጭቱ በሰላም እንዲቋጭ እያደረገች ያለውን ጥረት እና በፀጥታዉ ም/ቤት የወሰደችዉን አቋም አስመልክቶ ምስጋና አቅርበዋል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram