ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አንካራ

በሱዳን የሚገኙ የቱርክዬ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣትን አስመልክቶ ክቡር አምባሳደር አደም መሐመድ ከቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደቡብ እና የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ዳይሬክተር ጄኔራል ከሆኑት አምባሳደር ኤሊፍ ቾሞግሉጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡

የቱርክዬ ዜጎች በሰላም ከሱዳን እንዲወጡ ኢትዮጵያ ላበረከተችው ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ዳይሬክተር ጄኔራሏ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያና ቱርክዬ የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በቅርበት ተባብረው እንደሚሰሩ ተግባብተዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram