ሚያዚያ 02 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አንካራ

በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ በዋና ዋና የአገራችን ጉዳዮች ላይ በቱርኪዬ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካዮች ጋር በZOOM የበይነ-መረብ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን፣ የተጀመረው የሰላም ስምምነት አተገባበር፣ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 26-28 ቀን 2023 በአገራችን ስለሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረምና ስለ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ገለጻ አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደር በአገራችን የተጀመረው የሰላም ጎዳና ከግብ እንዲደርስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ያሳሰቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ንቁ ድጋፍ እና ተሳትፎ በማድረግ የአገራችንን የመስህብ ቦታዎች ለጎቢኝዎች ምቹ እና ተደራሽ እናድርግ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች በኩል ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፣ በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ የተጀመረውን የሰላም መንገድ ከግብ ለማድረስ እና በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት በሚችሉት ሁሉ በንቃት ለመሳተፍ እና ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram