መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም (አስታና)

ተቀማጭነታቸው በቱርክዬ አንካራ የሆኑት የኢፊዲሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም ሙሐመድ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 6 ቀን 2023 የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካዛኪሰታን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት H.E. Kassym Jomart Tokayev አቅርበዋል፡፡

ክቡር አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቢያቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት ከክብርት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት እና መልካም ምኞት አስተላልፈዋል፡፡

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ሲያቃርቡ ባደረጉት ንግግር በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም እንዲሁም የህዝብ ለህዝ ግንኙነቱን ለማጠናከር ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ በማከልም የኢትዮጵያ እና ካዛኪስታንን ግንኙነት ወደ ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማሳደግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ ክቡር ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እና እንዲያድ የመንግስታቸው ፍላጎት መሆኑን ገልጸው በዚህ ረገድ ክቡር አምባሳደር አደም መሐመድ ለሚያደርጉት ጥረት የመንግስታቸው ሙሉ ድጋፍ እና ትብብር የማይለያቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram