ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አንካራ
የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት Recep Tayyip Erdogan፣ የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ላደረጉት አፋጣኝ የነፍስ አድን ድጋፍ እና ትብብር ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ፣ ለክቡር አምባሳደር አደም መሐመድ እና ለኢትዮጵያ የነፍስ አድን ቡድን መሪ ሌ/ጄኔራል ደስታ አቢቼ ሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።
ባለፈው የካቲት ወር በቱርክ ከ59 ሺህ በላይ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከስቶ የነበረ ሲሆን÷ በሌ/ጄኔራል ደስታ አቢቼ የሚመራ የኢትዮጵያ የነፍስ አድን ልዑክም በቱርክ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡