ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም (አንካራ)

ህዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ኤምባሲ አንካራ በሚገኘው YUCE College ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል፣ ቱሪዝም፣ እንዲሁም የኢትዮ-ቱርኪዬ ግንኙነት አስመልክቶ የት/ቤቱ ተማሪዎች እና መምህራን በተገኙበት ሰፋ ያለ ገለጻ ተካሄዷል።

በገለጻው ወቅት አገራችን ጥንታዊ ታሪክ ያላት፣ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ አፍሪካዊትና የመጀመሪያው ሂጅራ የተካሄደባት አገር መሆኗ የተብራራ ሲሆን፣ ከቱርኪዬ ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላት መሆኗም ተገልጿል።

በተጨማሪም አገራችን የበርካታ ቋንቋዎች፣ እምነቶች እና ባህሎች ባለቤት፣ እንዲሁም ህዝቦቿ በመተሳሰብ እና በመከባበር የሚኖሩባት አገር መሆኗን በመጠቆም የአገራችን ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ አልባሳት፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የተብራሩ ሲሆን፣ በአገራችን የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች፣ እንዲሁም በUNESCO የተመዘገቡ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶች ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ባህላዊ ቡና አፈላል ስነስርዓት በማከናወን የኢትዮጵያን ታሪካ እና ባህል የሚያሳይ የስዕል እና ቁሳቁስ አውደ-ርዕይ የተካሄደ ሲሆን፣ በፕሮግራሙ ወቅት የአገራችንን ባህላዊ አልባሳት፣ ዳቦ እና ቡና የማስተዋወቅ ስራ ተከናውኗል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram