የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ ቡድን በቱርክ ጉብኝት አደረገ
********
ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም.
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ጄነራል አበባው ታደሰ የተመራው ወታደራዊ ልዑክ ቡድን የቱርክ ወታደራዊ ኃይል በክረምት ወቅት (Winter Season) የተጣለበትን አገራዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ግዳጅ ለመወጣት ያለዉን አቅምና ዝግጁነት ለማሳየት ከጥር 24-25 ቀን 2015 ዓ.ም. በምስራቅ ቱርክ በምትገኘው ካርስ ግዛት በተዘጋጀው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ተሳትፏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ልዑክ ቡድኑ የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ዘርፍ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመከር ይጠበቃል፡፡