ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም (የኢፌዲሪ ኤምባሲ፣ አንካራ)- አንካራ የሚገኘው የኢፌዲሪ ሚስዮን ከቱርኪዬ የንግድ ማህበረሰብ ማህበር ሙሲያድ (MUSIAD) ጋር በመተባበር የኢትዮ-ቱርኪዬ ቢዝነስ ፎረም አካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ክቡር የኢ.ፌ.ዲሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የኢትዮጰያ ኢንቨስንትመንት ሆልዲንግ ም/ስራ አስፈጻሚ ክብርት ያስሚን ወሃብረቢ፣ ፣ ክብርት አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ፣ የቱርክዬ የንግድ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ክቡር Mr. Mustefa Tuzcu፣ የMUSIAD ፕሬዝዳንት Mr. Mahmut Asmash እንዲሁም ከ300 በላይ የሚሆኑ የሁለቱ አገራት ባለህብቶች ተገኝተዋል።

በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር በማድረግ፤ የኢትዮጵያና የቱርክዬ ዘመናት ያስቆጠረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና የሁለቱን አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት መጠናከር በሚችልበት ሁኔታ በማስመለከት ንግግር አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መድረኩን ላዘጋጁ ተቋማት ምስጋና በማቅረብ ባደረጉት ንግግር፣ በአገራችን በርካታ የቢዝነስ እድሎች መኖራቸውን በመጥቀስ፤ የሁለቱ አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የቱርክዬ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል። ክብር አምባሳደር አክለውም ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ በርካታ ዘርፎችን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረጓን ገልጸዋል።

ክብርት ያስሚን በበኩላቸው በአገራችን ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በሚመለከት ገለጻ በማድረግ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እያደረገ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ፣ ማበረተቻዎች እንዲሁም አዳዲስ ህጎችን በማብራራት የቱርክዬ ባለሃብቶች በአገራችን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የሁለቱን አገራት የንግድ እንቅስቃሴ በሚመለከት የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አቶ ውቤ መንግስቴ ገለጻ አድርገዋል።

በቱርክዬ ወገን፣ የአገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ክቡር Mr. Mustefa Tuzcu እና የMUSIAD ፕሬዝዳንት Mr. Mahmut Asmash ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ በርካታ የኢንቨስትመንት እና የንግድ አማራጮች መኖራቸውን ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ ሰፊ ገበያ ያላት እና የአፍሪካ መዲና በመሆኗ በአገሪቱ ኢንቨስት ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመገንዘብ የቱርኪዬ ባለሃብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በአጽንኦት ተናግረዋል።

በመጨረሻም የሁለቱ አገራት ባለሃብቶች በመገናኘት የቢዝነስ ለቢዝነስ (B2B) ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የኢትየጵያ ባህላዊ ቡና አፈላል ስነስርዓት በማካሄድ የቡና ማቅመስ ፕሮግራም ተከናውኗል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram