ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በቱርኪዬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ከኤስኬሸር ቻምበር ኦፍ ኢንድስትሪ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሀገራችንን የኢንቨስትመንት እድል የሚያስተዋውቅ ፎረም በኢስኬሸር ተካሄዷል።

በፎረሙ በኤስኬሸርና አካባቢዉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪን፣ በኮንስትራክሽን፣ በኤነርጅ ፣ በግብርና እንዲሁም በኤክስፓርት የተሰማሩ ባለሃብቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኤስኬሸር ቻምበር ኦፍ ኢንድስትሪ ፕሬዚዳንት Mr. Celalettin KESİKBAŞ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ቻምበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ኩባንያዎችን በአባልነት በማቀፍ ከ70 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ በኤስኬሸርና አካባቢዉ የሚገኙ ባለሀብቶች ያቀፈና የኢንቨስትመንትና የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የዚህ አይነት ፎረም ከኤምባሲው ጋር በጋራ መዘጋጀቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ እንደሚረዳም ገልጸዋል።

በመቀጠል ንግግር ያደረጉት በቱርክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሀመድ ሲሆኑ በኢትዮጵያ እና በቱርክዩ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በማንሳት ያለዉን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ገልፀዋል። በቅርቡ በኢትዩጵያ የተካሄደዉን ዉጤታማ “የኢንቨስት ኢትዩጵያ ፎረም” ሀገራችን ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሳየ መሆኑን በማንሳት በፎረሙ የተሳተፍትን የቱርኪዬ ባለሀብቶችን አመስግነዋል። መሰል ፎረም በኤስኬሸር መዘጋጀቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን የንግድና ኢንቨስትመንት ሁኔታ ያጠናክራል ብለዋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ምቹ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ለቱርኪዬ ባለሃብቶች ጥሪ አቅርበዋል።

የሀገራችንን የኢንቨስትመንት እድሎች በፖወር ፓይንት የተደገፈ ገለፃ ያደረጉት የኢትዩጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንቨስትመንት አማካሪ ወ/ሮ ሂወት ሀይሉ ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታና ስለተደረጉ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች፣ የትኩረት መስኮች ፣ ያሉ ማበረታቻዎች እና እድሎች በስፋት አስረድተዋል። በመጨረሻም በኢንቨሰትመንት ወደ አገራችን ለመግባት ለሚፈልጉ የቱርክ ባለሀብቶች ሁሉ ፅ/ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በማጠቃለያ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ተሰጥቷል፣ የተናጠል ውይይትም ተደርጓል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram