መርሲን ጥቅምት 9 ቀን 2016ዓ.ም ፣

በቱርኪዬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ከመርሲን ንግድ ም/ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሀገራችንን የኢንቨስትመንት እድል የሚያስተዋውቅ ፎረም በመርሲን ከተማ ተካሄዷል።

በፎረሙ በመርሲንና አካባቢዉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪን፣ በግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በኤነርጅ ፣ እንዲሁም በኤክስፓርት የተሰማሩ  ባለሃብቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሲን የኢፌድሪ የክብር ቆንሱል የሆኑት Mr. Bulent, Mersin Elbeyli የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ የመርሲን ንግድ ም/ቤት(Mersin chamber ምክትል ፕሬዝዳንት Mr. Cem BUCUGE የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ፎረሙን ከአንካራ ኢምባሲ ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት መቻላቸዉን በመግለፅ በዚህ ረገድ ትብብር ያደረጉትን  አመስግነዋል። ለወደፊቱም በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ በመርሲንና አካባቢዉ የሚገኙ ባለሀብቶች በማነሳሳት ወደ ኢትዩጵያ በመላክ የኢንቨስትመንትና የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመቀጠል ንግግር ያደረጉት በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሐመድ በቅርቡ የተካሄደዉን 4ኛዉ የቱርክ- አፍሪካ የቢዝነስና የኢኮኖሚ ፎረም በተሳካ ሁኔታ መካሄድኑ በማንሳት መሰል ፎረም መዘጋጀቱ በኢትዩጵያና በቱርክዩ መካከል የተጀመረዉን የንግድና ኢንቨስትመንት ሁኔታ ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል። በመጨረሻም በኢንቨሰትመንት ወደ አገራችን ለመግባት ለሚፈልጉ የቱርክ ባለሀብቶች ሁሉ ኢምባሲዉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በመቀጠልም የሀገራችንን የኢንቨስትመንት እድሎች በፖወር ፓይንት የተደገፈ ገለፃ ያደረጉት በቱርክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታና ስለተደረጉ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች፣ የትኩረት መስኮች ፣ ያሉ ማበረታቻዎች እና እድሎች በስፋት አስረድተዋል።

ጠቃሚ የሎጂስቲክ ማዕከል እና የወደብ ከተማ የሆነችው መርሲን በግብርና እና በምግብ ኢንዱስትሪዎች፣ በቱሪዝም እና በሎጂስቲክስ ዘርፎች የአገሪቱ በጣም አስፈላጊ የኢኮኖሚ ልማት ማዕከላት የሆነች ከተማ ናት።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram