መስከሪም 24 ቀን 2015 ዓ.ም ካይሰሪ፣

በቱርኪዬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ከካይሰሪ ቻምበር ኦፍ ኢንደስትሪ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሀገራችንን የኢንቨስትመንት እድል የሚያስተዋውቅ ፎረም በካይሰሪ ከተማ ተካሄዷል።

በፎረሙ በካይሰሪና አካባቢዉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪን፣ በኮንስትራክሽን፣ በኢነርጅ ፣ እንዲሁም በኤክስፓርት የተሰማሩ ባለሃብቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የካይሰሪ ኢንዱስትሪ ም/ቤት (KAYSO) የቦርድ አባል የሆኑት Mr Ahmet Ezinç. የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው ፎረሙን ከኤምባሲ ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት መቻላቸዉን በመግለፅ በዚህ ረገድ ትብብር ያደረጉትን አመስግነዋል። ለወደፊቱም በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ በካይስሪና አካባቢዉ የሚገኙ ባለሀብቶች በማነሳሳት ወደ ኢትዩጵያ በመላክ የኢንቨስትመንትና የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመቀጠል በየተራ ንግግር ያደረጉት Mr Erol Sırıklı በካይሳሪ ንግድ ም/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እና ኢደባሊ ካራሙስታፋኦግሉ ሲሆኑ ሁሉም በኢትዩጵያና በቱርክዩ መካከል የቆየዉን ታሪካዊ ግንኙነት በማንሳት ይበልጥ በንግድና ኢንቨስትመንት ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።

በቱርክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ በመክፈቻ ንግግራቸዉ በኢትዮጵያ እና በቱርክዩ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በማንሳት ያለዉን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ገልፀዋል። ቀደም ሲል በተለያዩ የቱርክዩ ከተሞች ፎረም በትብብር መዘጋጀቱን በማስታወስ በካይሰሪ መሰል ፎረም መዘጋጀቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን የንግድና ኢንቨስትመንት ሁኔታ ያጠናክራል ብለዋል።

በመቀጠልም የሀገራችንን የኢንቨስትመንት እድሎች በፖወር ፓይንት የተደገፈ ገለፃ ያደረጉት ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታና ስለተደረጉ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች፣ የትኩረት መስኮች ፣ ያሉ ማበረታቻዎች እና እድሎች በስፋት አስረድተዋል። በመጨረሻም በኢንቨሰትመንት ወደ አገራችን ለመግባት ለሚፈልጉ የቱርክ ባለሀብቶች ሁሉ ኢምባሲዉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል።
በአገራችን ውስጥ ኢንቨስት ካደረጉ የቱ ርክ ካምፓኒዎች መከከል ኩምቴል በአገራችን ኢንቨስት ምቹ ስለመሆኗ
ለፍረሙ ታሚዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ከፎረሙ በኃላ በቱርክዩ ትላልቅ የሆኑ 3ዐዐ በላይ የሆኑ የፈር ኒቸር አምራች ኩባንያዎች ሰብሰብ ከሆነው Kumsmall ጉብኝት በማድረግ ከቦርዱ ሊቀመንበር ከሆኑትMr Erca SARJKAY እና ሌሎች የቦርድ አባት ጋር ዉይይት ተደርጓል። በውይይቱም በአገራችን ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲያዮ በተገለፀላቸው መሰረት በቀጠይ በአገራችን ያለውን አማራጭ ለማየት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

Kumsmall በቱርክ ካሉ የመጀመሪያ ከአንድ እስከ Uያ ያሉ ከፍተኛ አቅም ያላቸው የፈርኒቸር አምራች ድርጅቶች ያቀፈ እና ከ300 በላይ የፋርኒቸር ኩባንያዎች ያሉት ትልቁ ሞል ነዉ።

በመጨረሻም በቱሪክ በተለያዮ ከተሞች coffee shop በመክፈት የአገራችንን ቡና በካይሰሪ የሚያስተዋውቀውን “አዲስ አበባ coffee shop“ በመጎብኘት ባለሀብቱን አበረታትናል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram