ግንቦት 14/2015 (አንካራ)

በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አደም መሐመድ በቱርክ አንካራ ከተማ የሚገኘው INCELER MEDIKAL የኩላሊት ጠጠር በshock wave therapy ለማከም የሚረዱ መሳሪያ አምራች የሆነው (INC MEDIKAL LTD) ኩባንያ ጉብኝት አደረጉ፡፡

በጉኝቱም ወቅት ከ INCMEDIKAL LTD ድርጅት ማናጀር ከሆኑት Mr Mehmet INICE እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ድርጅቱ ከ50 በላይ ሰራተኞች እንዳሉት፣ ከ13 ዓመታት በላይ ልምድ እንዳለው፣ ምርቱን ለተለያዩ አውሮፓ አገራት እንደሚልክ እና የኩባንያው ዋና ዋና ምርቶች የኩላሊት ጠጠር በጨረር ለማከም የሚረዱ መሳሪያዎች Extracorporeal shock wave therapy (ESWL)፣ የኑሮሎጂ፣ ፊዚዮትራፒ) ማሽን በማምረት እና ምርቶቹን ለተለያዩ ሆስፒታሎች የሚያቀርብ ካምፓኒ ነው።

በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ስላለው ሁኔታ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ በዚሁ ዘርፍ ስላለው ገበያ ለማጥናትና ለወደፊቱ በማምረት ተግባር መሰማራት እንደሚፈልጉ መረዳት ተችሏል ፤ ከገለጻውም በመቀጠል ፋብሪካው የሚያመርታቸው ምርቶች ጉብኘኝት ተደርጓል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram