TURKEY — AFRICA BUSINESS FORUM – “Export Gateway to Africa “ በሚል ከDecember 17 – 19/2022 በኢስታንቡል ከተማ Istanbul Expo Center ተካሂዷል።
ቢዝነስ ፎረሙ በኢስታንቡል ትልልቅ ኤግዚብሽኖችንና የንግድ ትርኢቶችን በማዘጋጀት በሚታወቀው CNR HOLDING ኩባንያ አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን ከ200 በላይ የሚሆኑ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ሲያስተዋውቁ ከ5000 በላይ ጐብኝዎች ደግሞ ተሳታፊ ሆነዋል። በኤግዚብሽኑ ላይ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ የዋሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች፤ የተለያዩ ማሽነሪዎች፤ በኢነርጂ፤ በፈርኒቸር፤ በጨርቃጨርቅ፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፤ ፕሪፋብሪክ የቤት እቃዎች፤ የተለያዩ የግብርና መሳሪያዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ምርቶች ጉብኝት ተካሂዷል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በቱርክ የኢፌዴሪ ኤምባሲ የአገራችንን የተለያዩ የወጪ ምርቶች, ቡና፤ ሰሊጥ፤ ሽምብራ፤ ቦሎቄ፤ ማሾ፣ እንዲሁም የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን ለእይታ በማቅረብ የማስተዋወቅና የገበያ ትስስር የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡ በተጨማሪም የአገራችንን የቱሪስት መስቦችና የቱሪዝም ሀብቶችን እንዲሁም የአገራችን መለያ የሆነውን የቡና አፈላል ስነስርዓት ለጐብኝዎች ማስተዋወቅ ተቸሏል፡፡
በኢንቨሰትመንትም በአገራችን የትኩረት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችን በመለየትና በማነጋገር በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram