ህዳር 24 ቀን 2017 (አንካራ): በቱርክዬ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሀመድ በቱርኪዬ/ ኤስኬሸር ከሚገኘው ASKON ማህበር የቦርድ አባላት ጋር በሀገራችን ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮች አስመልክቶ በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አካሄደዋል ።
በውይይቱም በሀገራችን ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና መንግስት በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ የውጭ ኢንቨስተሮች እያደረገ ስላለው ማበረታቻዎች አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።
ባለሀብቶቹም በበኩላቸው ASKON በቱርኪዬ ከ15 ሺህ በላይ በኤስኬሽር ደግሞ ከ100 መቶ በላይ አባላትን የያዘ ማህበር መሆኑንና አባላቶቹም በቱርኪዬ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እያደረጉ እንደሆነ በማንሳት በተደረገላቸዉ ገለፃ አመስግነዉ በቀጣይም በአገራችን በኮንስትራክሽን ፣በግብርናው፣በኢነርጂ ፣በማኑፋክቸሪንግ እና በንግዱ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ በአገራችን ያለውን አማራጭ ለማየት ወደ አገራችን መሄድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከባለሀብቶቹ ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ፤ በቀጣይም ለማህበሩ አባላት በአገራችን ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ ለማድረግ በእስኬሸር ፎረም ለማዘጋጀት መግባባት ተፈጥሯል።