ጥቅምት 06 ቀን 2017 (ኢስታንቡል)፡ 11ኛው የአለም አቀፍ ትብብር ፎረም (WCI) በኢስታንቡል በ WOW ኮንግረስ ሴንተር እኤአ ከኦክቶበር 16-17 ቀን 2024 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን “Africa is the future; the future is in Africa “በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ነዉ።

የፎረሙ ዋና አላማ በቱርኪዩና አፍሪካ ንግድ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግና አነስተኛና መካከለኛ (SMS) አምራቾችን በማስተዋወቅ ለማበረታታት ነዉ። በተዘጋጀው መድረክ ላይ በኮንስትራክሽን፣ጨርቃጨርቅ፣ ምግብ፣ ግብርና፣ መለዋወጫና ሎጂስቲክስ የተሰማሩ ከ200 በላይ የተለያዩ የቱርክ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን አስተዋውቀዋል የB2B ዉይይቶች ተካሂደዋል። በፎረሙ ከ50 የአፍሪካ ሀገራት የተጋበዙ የኩባንያ ባለቤቶች ተገኝተዋል።

በተካሄዉ ፎረሙ ላይ የክብር ሀገር (Honored Guest Country) የሆነችው ጋና ስትሆን በጋና ሪፐብሊክ የRoads and Highways ሚኒስተር በሆኑት FRANCIS ASENSO-BOAKYE የተመራ ከ100 በላይ ባለሀብቶች ቡድን በፎረሙ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በተዘጋጀዉ ፎረም ላይ የቱርክዩ የንግድ ሚኒስቴር PROF. DR. ÖMER BOLAT፣ የWCI የቦርድ ሊቀመንበር PROF. DR. ABDÜLKADIR DEVELÌ፣ የWCI ፕሬዝዳንት UTKU BENGiSU በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቱርኪዩ ተቀማጭ የሆኑ የአፍሪካ አምባሳደሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።

በፎረሙ በአንካራ የኢፌድሪ ሚስዩን ተሳትፎ በማድረግ ከተለያዩ የስራ ሀላፊዎችና ባለሀብቶች ጋር ዉይይት ተደርጓል። እኤአ ጁን 2025 ተመሳሳይ ፎረም በኢትዩጵያ ለማካሄድ ከፎረሙ ፕሬዝዳንት ጋር ዉይይት በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሳል።

WCI Forum ከ12 አመት በፊት የተቋቋመ፣ ከ54 አገሮች ጋር በትብብር የሚሰራ፣ ከ60 ግዜ በላይ ኢግዚቪሽንና ፎረሞችን ያዘጋጀ እንዲሁም ከመንግስት እና ሌሎች ማህበራት ጋር በትብብር የሚሰራ ድርጅት ነዉ።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook