የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም
127ኛው የአድዋ ድል ቀን “የአድዋ ድል በዓል ለአገራዊ አንድነት፣ ጀግንነትና ፅናት መልህቅ” በሚል መሪ ቃል ቱርኪዬ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ በቱረኪዬ የሚኖሩ ኢትዮጵውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት፣ በፓናል ውይይት በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
የዓድዋን ድል በተመለከተ የጦርነቱን መንስዔዎች፣ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ትግል፣ የጦርነቱ ሂደትና የኢትዮጵያውያን ጀግኖች የነፃነት ተጋድሎና የድሉን ትሩፋቶች የሚያወሳ የመነሻ ጽሁፍ በቱርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ ቀርቦ የፓናል ውይይት ተደርጓል።
ክቡር አምባሳደር ባቀረቡት ጽሁፍ፣ የአድዋ ድል አገራችን ነጻነቷንና ክብሯን ጠብቃ አንድትቆይ ከማድረጉም ባሻገር፣ በተቀረው ዓለም በቅኝ አገዛዝ የባርነት ቀንበር ውስጥ ለነበሩ ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ደወል በመሆን፣ አብዛኞቹ አገራት ነፃነታቸውን እንዲቀዳጁ ምክንያት የሆነ አኩሪ ታሪካችን መሆኑን ገልጸዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የበዓሉ ታዳሚዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቅርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም፣ ጥንት አባቶቻችን ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለው ያቆዩትን አገር ሉዓላዊነት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ይህችን ሀገር ወደ ብልጽግና ማማ ማድረስና በክብር የምትታይ የአፍሪካ ዕንቁ ማድረግ የዚህ ትውልድ ግዴታና አደራ መሆኑ በውይቱ ወቅት ተብራርቷል።
The 127th anniversary of the victory of Adwa warmly celebrated at the Embassy of Ethiopia in Ankara in the presence of staffs and Ethiopian community.
H.E. Adem Mohammed, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of Ethiopia to Türkiye, emphasized in his speech that the victory of Adwa is a symbol of Unity, Bravery and Perseverance not only for Ethiopian but also for all black people across the world.
He underlined that just like our forefathers, the new generation of Ethiopia must repeat history marching in unison on our current enemy; Poverty, Backwardness and Hunger. In order to build prosperous country, he also urges all Ethiopians to work hand in glove. He added that as we always fought tooth and nail to defend the unity and territorial integrity of the country, Ethiopian`s should enhance their synergy and resources to climb the ladder of prosperity.

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram