ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም (አንካራ)
በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ልዮ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሐመድ፣ በሞስኮ የኢፌዲሪ ልዮ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ቻም ኡጋላ፣ የሚስዮኑ ምክትል መሪ ሙሌ ታረቀኝ (አምባሳደር)፣ የሚስዮኑ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 18ተኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
![](https://ankara.mfa.gov.et/wp-content/uploads/2023/12/nation-1-300x225.jpg)
በመጨረሻም የበዓሉ መሪ ቃል ትንተና ዙሪያ ከኢፌዲሪ የፌደሬሽን ም/ቤት የተላከ ሰነድን መሰረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል።