ማርች 21፣ 2023 ኢስታንቡል
8ኛው የአለም የትብብር ኢንዱስትሪዎች ፎረም ከማርች 21-22/2023 “Africa is future, future is Africa” በሚል መሪ ቃል በኢስታንቡል በሚገኘው ዋው ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ከ54 አገሮች የተውጣጡ ተጋባዥ የኩባንያ ባለቤቶች እና ከ400 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች ምርቶቻቸዉን ያቀረቡ ሲሆን፣ ከ1,500 በላይ ተሳታፊዎች በፎረሙ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የፎረሙ ዋና አላማ በቱርክና በአፍሪካ ነጋዴዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ እና የቱርክ መካከለኛና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ምርቶችን ማስተዋወቅ ሲሆን፣ የተለያዩ የቱርክ ኩባንያዎች እንደ ኮንስትራክሽን፣ ጨርቃጨርቅ፣ ምግብ፣ ግብርና፣ መለዋወጫና ሎጂስቲክስ የመሳሰሉ ምርቶቻቸውን አቅርበዋል።
በፎረሙ ላይ ከኢትዮጵያ ወደ 20 የሚጠጉ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች፣ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ከቱርክ አቻዎቻቸው ጋር B2B ዉይይት አድርገዋል። በፎረሙ ላይ ምክትል የሚስዩን መሪ አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ ተሳትፈዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram