ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም (በአንካራ የኢፌዲሪ ሚስዮን) – በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ሚስዮን አንካራ የሚገኘው ሐጂቴፔ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው እና ከ20 በላይ የሚሆኑ በቱርኪዬ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ሚስዮኖች የተሳተፉበት የዓለም አቀፍ የወዳጅነት ቀን ላይ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን፣ በበዓሉ ወቅት የተለያዩ አገራት ታሪክ፣ ባህል፣ ባህላዊ ቅርሶች እና የቱሪዝም ስፍራዎች ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለዕይታ ቀርቧል።

በበዓሉ ወቅት ሚስዮናችን የኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን፣ ባህላዊ አልባሳትን፣ የቱሪዚም ቦታዎችን እና በዩኔስኮ የተመዘገቡ የኢትዮጵያ የዓለም ቅርሶች ለዕይታ ያቀረበ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎችን በማስተባበር የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል፣ የቱሪዝም ቦታዎችና ቅርሶች አስመልክቶ ለበዓሉ ታዳሚዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት በማካሄድ ለታዳሚው የአገራችንን ቡና የማቅመስ ፕሮግራም እንዲሁም ኢትዮጵያ የቡና መገኛ አገር መሆኗን ማስተዋወቅ ተችሏል።

በመጨረሻም በበዓሉ ከታደሙ የተለያዩ አገራት ሚስዮን ተወካዮች ጋር የባህል ልውውጥ እና ውይይቶች ማካሄድ የተቻለ ሲሆን፣ ከሐጂቴፔ ዩኑቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ጋር ግንኙነታችንን ይበልጥ በምናጠናክርበት ሁኔታዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram