ጥር 9 ቀን 2016 ዓ/ም (አንካራ)

በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ አፈወርቅ ሽመልስ በኢስታንቡል ከተማ ከሚገኘው የ“HALAL EXPO” ዓለምአቀፍ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ከሆኑት Mrs.Wassila OULDCHIKH ጋር ዉይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ የ “HALAL EXPO” ዓለምአቀፍ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት Mrs.Wassila OULDCHIKH በበኩላቸው ስለ ኤክስፖው በሰጡት ማብራሪያ “Halal Expo 2023” እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 23-26 /2023 በኢስታንቡል Expo Center እንደተካሄደ እና በኤክስፖውም ከ 100 አገሮች የመጡ ከ30 ሺ በላይ ነጋዴዎች በመሳተፍ የልምድ ልውውጥ ያደረጉበት ትልቅ የኤክስፖ መድረክ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ በሚዘጋጀው ኤክስፖ የአገራችን የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሣተፉ ጠይቀዋል ።

በመሆኑም ሚሲዮናችን በቀጣይ በሚዘጋጀው ኤክስፖ የአገራችንን የኢንቨስትመንት አማራጮች በቱሪዝም መዳረሻዎች ፣ በባህል እና የአገራችንን የወጪ ምርቶችን ለማስተዋወቅ በትብብር እንደምንሰራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram