128ኛው የዐድዋ ድል በዓል በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ሚስዮን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፤ ************************************** የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም (አንካራ) 128ኛው የአድዋ ድል በዓል “አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በቱርኪዬ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ እንዲሁም የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች በተገኙበት በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በዓሉን አስመልክቶ ክቡር አምባሳደር አደም መሐመድ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ነጠላ ትርክቶች ሳንጎተት እንደ ዓድዋ ድል የመሳሰሉ የጋራ አገራዊ ገዥ ትርክቶች ላይ በማተኮር መንግስት እያከናወናቸው የሚገኙትን ዘርፈ ብዙ የልማት እና ሰላምን የማረጋገጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ሁላችንም ኃላፊነታችንን በመወጣት ድህነትን ለመቀነስ ፣ ሰላምን ለማስፈንና የአገራችንን ብልጽግና እውን ለማድረግ የበኩላችንን አዎንታዊ ሚና መጫወት እንዳለብን በአፅንኦት አሳስበዋል። በፕሮግራሙም የዓድዋን ድል የሚዳስስ ዶክመንተሪ ፊልም ለዕይታ የቀረበ ሲሆን፣ የበዓሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ የተሳተፉበት የፓናል ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ክቡር አምባሳደር ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል። በተጨማሪም በቱርኪዬ እና ኤምባሲው በሚሸፍናቸው አገራት የሚገኙ ኢትየጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ያሳተፈ የበይነ-መረብ ውይይት ተካሂዷል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram